የምረቃ ፕሮግራም ላይ ተገኝተዉ መክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ልማት ማህበር ምክትል ዳይሬክተርና የግምገማና ክትትል ክፍል ኃላፊ ሀጂ በድሩዘማን አብደላ እንኳን ለዚህ ቀን አደረሰን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ።

የካፋ ዞን የትምህርት መምሪያ የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆኑ ትምህርት ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ጀማል አባመጫ እንዳሉት የተሻለ ትዉልድ ለመፍጠር የወላጆች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው ተማሪዎችም ጠንክረው በቀጣዩ ክፍል ላይ የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ መቻል አለባቸዉ ብለዋል ።

በካፋ ልማት ማህበር ፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ተወልደብርሃን እንዳሉት የካፋ ልማት ማህበር ጄኔቫ ግሎባል ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረ – ሰናይ ድርጅት ጋር በትምህርት ላይ አብሮ ለመስራት ሲወስን ፣ ድርጅቱ በአገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች እና ዞኖች ላይ በተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ላለፉት 10 ዓመታት ከመጥቀም ባለፈ የካበተ ልምድ ያለውና የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎችንም በአገራችን በትምህርት ዘርፍ ዉጤታማ የሆነ ድርጅት መሆኑን በማረጋገጥም መሆኑን ተናግረዋል::

የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አክለዉም የጄኔቫ ግሎባል ኢትዮጰያ አላማ በተለያዩ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ምክንያት የመደበኛ ትምህርታቸውን መማር በሚገባቸው የዕድሜ ክልል ላይ እያሉ ሳይማሩ ያለፉትን ዕድምያቸው ከ 9- አስፈላጊውን 14 ዓመት የሚደርሱ ህጻናትን ወደ ትምህርት ገበታ በማምጣት የትምህርት ግብአት እና ወላጆቻቸውን አልያም አሳዳጊዎቻቸውን በመደገፍ በተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም ህጻናትን በ 10 ወራት ዉስጥ ለ4ተኛ ክፍል የማድረስ ዓላማ ያለው ድርጅት ነው ብለዋል::

ድርጅቱ በአገራችን የትምህርት ሚኒስትር የብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ያገኘ እና በተለያዩ ክልሎች ብዛት ያላቸውን ዜጎች በመጥቀም ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን ከዓመት ዓመት ተደራሽነቱን እያሰፋ ባሳለፍነው የትምህርት ዘመን ዕድሉን ለካፋ ዞን በመስጠት በዞናችን በ 2 ወረዳዎች ማለትም በቦንጋ እና በጎባ ወረዳ ለሚገኙ 5 ትምህርት ቤቶች

ዕድሉን በመስጠት 180 ተማሪዎችን የዕድሉ ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል።

በቦንጋ ከተማ የዕድሉ ተጠቃሚ ትምህርት ቤቶች መካከል የባንዲራ 1ኛ ደ/ት/ቤት እና የሽታ 1ኛ ደ/ት/ቤት ሲሆኑ

በጎባ ወረዳ ዪሊዮ 1ኛ ደ/ት/ቤት፣ አዲስ ፋና ት/ት/ቤት እና ኡዳ ሻከራ 1ኛ ደረጃ ትም/ት/ቤት መሆናቸዉን ተናግረዋል::

የተማሪዎችን ብዛት በተመለከተ ወንድ 96 ሴት 85 በድምሩ 180 የሚሆኑ በዚህ ፕሮግራም ትምህርታቸውን

ለመከታተል ተመዝግበዋል ብለዋል::

በዚህ ፕሮጀክት በድርጅቱ በኩል የተደረጉ ድጋፎችን በተመለከተ ለአምስቱ ትምህርት ቤቶች አመቻች መምህራንን በመቅጠር ላለፉት 10 ወራት ስልጠናዎችን በመስጠት እና የመምህራኖችን የወር ደመዎዝ በመክፈል ስራው እንዲሰራ ማድረግ አመቻቾችን ጨምሮ 29 የመደበኛ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራኖችን በተፋጠነ የትምህርት ፕሮግራም የትምህርት አሠጣጥ ሂደት ላይ የአንድ ሳምንት ስልጠና እንዲወስዱ ተደርጓል ብለዋል::

በአምስቱም ትምህርት ቤቶች ላይ ትምህርታቸውን ለመከታተል ለተመዘገቡ 180 ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ እርሳስ-ላጲስ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ መሳርያ የመሳሰሉትን ላለፉት 3 ተከታታይ ክፍሎች በማማሏት ማስመርያ እና ትምህርታቸውን ሳይቸገሩ እንዲማሩ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል::

የመማር ማስተማር ሂደቱን የተሳካ ለማድረግ እንዲረዳ ወቅታዊ ክትትል እና ድጋፍ የሚያደርጉ 2 ሱፐርቫይዘሮችን እና 1 ፎካል ፐርሰን ከልማት ማህበሩ እንዲመደቡ ማድረጉን የተናገሩት አቶ ገዛሃኝ 89 ለሚሆኑ የተማሪ ወላጅ እናቶች በፈለጉት የስራ መስክ ላይ ተሰማርተው መንቀሳቀስ እንዲችሉ የማይመለስ የስራ ማስጀመርያ የገንዘብ ድጋፍ ለ 5 ማህበራት እና 89 አባላት ተደርጓል ብለዋል::

ከዚህ ጎን ለጎን ለፕሮጀክቱ መሳካት የካፋ ልማት ማህበር የነበረው ድርሻ ቀላል የማይባል ሚና መሆኑንም ተናግረዋል::

ለዚህ ስራ ዉጤታማ እንድሆን ትብብር ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት እና የተሻለ ዉጤት በማስመዝገብ 1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ለወጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማ ተበርክቷል።