የካፋ ዞን ምክትል አስተዳደር ክቡር ደመላሽ ንጉሴ እና የካልማ ዳሬክተር አቶ ይገዙ ቡርሃኑ በተገኙበት ስብሰባው በአባቶች ምርቃት ተጀምሮ በእለቱ ከተገኙ ተሳታፊዎች ጋር ጥልቅ ውይይት ተድርጓል።

የልማት ማህበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ ቀደም ተመስርቶ ተቋሟዊ ግዴታ ሲወጣ የቆየ ቢሆንም በተለያየ ምክንያት ተቀዛቅዞ ና ተቋርጦ ቆይቷል ::

ለዚህም በእለቱ የተገኙ ተሳታፊዎች ምክንያት ይሆናል ያሉትን ሀሳብ እና አስተያየታቸውን ሰተዋል :: ይሁን እንጂ አሁን እንደገና ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ማጠናከር ህዝቡን አሰባስቦ እምቅ አቅምን ለልማት ማዋል አስፈላጊ ሆኗል።

ስለዚህ ልማት ማህበሩ በተለያዩ ከተማዎች ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን እያቋቋመ እና እያጠናከረ በመሆኑ የሚዛን አማን ከተማ የካልማ ቅ/ጽ/ቤትንም እንደገና ማደራጀትና ማጠናከር ም የዚሁ እቅድ አካል ነው።

የልማት ማህበሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ተጠናክሮ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ሰባት አባላት የያዘ ግዜአዊ አስፈፃሚ ኮሚቴዎችን በመምረጥ ጉባኤው ተጠናቋል።