የካፋ ልማት ማህበር ከቡና ሚዲያ ና ኮምንኬሽን ጋር በመተባበር ተዘጋጀ ፕርግራም በ አዲስ አበባ ልደታ ስማርት ፕላዛ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ተገኝተዉ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ በንግግራቸዉ ትዉልድ የማይረሳዉን የሻተራሻ ገሮ ስራን ለመስራት የቡና ሚድያና ኮሚዩኒከሽን ባልቤት አቶ አማኑኤል ኃይሌ ጋር እንዲሁም ከካፋ ልማት ማህበር ጋር በመነጋገር አጠቃላይ ስራዎቹን የሚዳስስ ዶክሜንታሪ ተሰርቶ ለእይታ መብቃት መቻሉን ተናግረዋል ።

ምሁራን በካፋ ባህልና ታሪክ ላይ የሚያጠነጥን ስራዎችን ትኩረት ሰተው እንዲሰሩ የጠየቁት አስተዳዳሪዉ አስፈላጊዉን ድጋፍ የዞን መንግስት እንደሚያደርግ ጭምር ነዉ የገለፁት ::

የሻተራሻ ገሮ ገብሬ ቤተሰቦች፣ የኢፈድሪ የመንግስት ግዥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ገብሬ ማርያም የካፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደን ጨምሮ የአዲስ አበባ ካፋ ተወላጅ ነዋሪዎች የቡና ሚዲያና ኮምንኬሽን ባለቤት አቶ አማኑኤል ኃይሌ ካፋ ዞን ባህል ምክር ቤት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች እየተሳተፉ ይገኛሉ ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ በበኩላቸዉ ለዛሬው ቀን ከረዥም ጊዜ በኃላ ለእይታ የበቃዉና ከልጅነት ጀምሮ አከባቢዉን ሲያስተዋውቅ በታወቁና ተፅእኖ ፈጣሪ ሰዎቹ በተለይም በካፋዎች ዘንድ ኖ ዎራፎ ካፍኔ በሚለዉ ዘፈኑ የሚታወቀዉ ዶክመንታሪ ስራን አስታዉሰዉ ለሰራ ለካፋ ዞን መንግስት ለእይታ እንዲበቃ ላደረጉት የቡና ሚዲያና ኮሚዩኒከሽን ባለቤት አቶ አማኑኤል ኃይሌና የካፋ ልማት ማህበርን አመስግነዋል ።

ዶክተር አክለው እንደዚህ አይነት ተፅዕኖ ፈጣሪና የሀገር ባለዉለታ የሆኑ ሰዎችን ለመዘከር ሁሉም ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም አሳሳበዋል።

የሻተራሻ ገሮ ገብሬ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት አቶ መኩርያ

ለሁሉም በሚገባ ቋንቋ በሚገባና ትምቢታዊ ዘፈኑ የሚታወቀዉ የሻተራሻን አስቦ የሰሩትን አካላትን አመስግነዋል ።

አቶ መኩርያ እንደዚህ አይነቱ ስራ የካፋን ባህል ታሪክና ቋንቋን ለትዉልድ ትዉልድ የሚያስተላለፍ ስራ በመሆኑ ዛሬ ትኩረት በመሰጠቱ ደስ የሚያሰኝ ነዉ ያሉት የሻተራሻ የቅርብ ጓደኛዉ ሁላችንም እንደዚህ አይነት ስራዎች ላይ ድጋፍና ክትትል ማድረግ ያስፈልጋል ነዉ ያሉት ። ታሪካችን ገና ብዙ ያልተዳሰስ በመሆኑ በትኩረት ሊሰራ ይባል ብለዋል።

የካፋ ልማት ማህበር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ይገዙ ብርሃኑ ካፋ ልማት ማህበር የካፋ ቋንቋን ባህል ታሪክ ለማሣደግ እንዲሁም ለሌሎች ለማሣወቅ እናም ሣይጠፋ ሣይበረዝ ለማቆየት ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ለማሥቻል እንዲህ አይነት ዶክመንታሪዎች መዘጋጀት እንዳለባቸውና ልማት ማህበሩም የበኩሉን ድርሻ እየተውጣ መሆኑን አክለው ገልፀው የሻተራሻ ገሮ ገብሬ ዶክመንታሪ ለዚህም ማሣያ ነው ብለዋል።

ዶክተር ሀመልማል ገሮ። ገብሬ በበኩሏ ዘመን ተሻጋሪና ትምቢታዊ ስራ ተደፍኖ እንዳይቀር ትኩረት ሰጥቶ ለዚህ እንዲበቃ ላደረገው ካፋ ዞን መንግስት ካፋ ልማት ማህበር ለቡኖ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ባለቤት አቶ አማኑኤል ኃይሌ እንዲሁም በስራው ላይ የተሳተፉትን በሙሉ አመስግነዋል።

አባቴ ሀገር ወዳድ ነዉ ያለች ዶክተር ሀመልማል እኛም ልክ እንደሱ አይነት ተግባራትን የመፈፀም ሃገራዊ ግዴታ አለብን ። ሁላችንም የካፋና አከባቢያዊ ልማት ላይ በትኩረት በመስጠት የየራሳችን አስተዋፅኦ በማድረግ አከባቢያችንን ማሳደግ አለብን ብለዋል ። ሰላሳ ደቂቃ የፈጀዉና በሻተራሻ ገሮ ገብሬ ታሪክ ላይ የተሰራ ዶክሜንታሪይ ለእይታ በቅቷል።

በመድረኩ ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል ዶክተር አሸብር ወልደ ጊዮርጊስ የኢፈድሪ የመንግስት ግዥ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ክፍሌ ገብሬ ማርያም የካፋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻዉ ከበደ የካፋ ልማት ማህበር ዳይሬክተር እና ከማኔጅመንት አባላት የተውከሉ የሻተራሻ ገሮ ገብሬ ልጅ ዶክተር ሀመልማል ገሮን ጨምሮ የአዲስ አበባ ካፋ ተወላጅ ነዋሪዎች የቡና ሚዲያና ኮምንኬሽን ባለቤት አቶ አማኑኤል ኃይሌ ካፋ ዞን ባህል ምክር ቤት አባላትና ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተሳትፈዋል እንዱሁም ለዚህ ዶክመንታሪ ጥናት መሳካት ልዩ ልዩ ድጋፍ እና እገዛ ላደረጉ አካላት የምስክር ወረቀት ተሰቷል።